•  አገልግሎቱን ለማግኘት ሲያመለክቱም ሆነ ሲረከቡ በአካል ወደ ኤምባሲ መቅረብ የግድ አይጠበቅብዎትም። በመሆኑም አገልግሎቱን የምንሰጠው በዋናነት በፖስታ ቤት በኩል ተረክበን የምናስተናግድዎ በመሆኑ ወደ ኤምባሲው ሲልኩም ሆነ የተዘጋጀልዎትን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወደ እርሶ መልሰን  ለመላክ ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number ባለው FEDEX ወይም  UPS   ይጠቀሙ። ኤምባሲው መታወቂያ ካርድዎ ከኢትዮጵያ እንደተረከበ በተቻለ ፍጥነት ይልክልዎታል።
  • የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ መታወቂያ ካርዱን በጊዜው ካላሳደሱ መቀጫ ስላለው እባክዎ የአገልግሎት ዘመኑ ሳያበቃ መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ፡፡ነገር ግን ቅጣቱ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ቢሆንም የመታወቂያው የአገልግሎት ዘመን ከማብቃቱ በፊት ማሳደስ እንደሚገባዎ አይዘንጉ!!!
  • የአገልግሎት ዘመኑ እስካላበቃ ድረስ  መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት ይችላሉ፡፡
  • የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም አዲሱን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡
 • እባክዎ ከጉዞዎ ወይም ከታደሰ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ 45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡

የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ

ሀ. የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርዱን ሲጠይቅ

ለ. አካለ መጠን ላልደረሰ  የኢትዮጵያ ተወላጅ  ልጅ ስለሚሰጥ አገልግሎት፤

ሐ. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሲጠይቁ

መ. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ሲጠይቁ

ሠ. በጠፋ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ

ረ. በተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ምትክ ሲጠይቁ


 ሀ. የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርድ ሲጠይቅ፣

1. መጠየቂያ ቅጽ-1 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)
2.የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት(አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት)ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
  የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ ፣
3.በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ማስረጃ፣

 • የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ማንዋል(ሰማያዊ)ከሆነ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ፎቶግራፍ፣ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ዋናውን ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ ማያያዝ፤ ወይም
 • የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ አዲሱ ማሽን ሪዴብል(ቀይ ቡኒ)ከሆነ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ፎቶግራፍ፣ፓስፖርቱ የተሰጠበትና  የአገልግሎት ጊዜው ያበቃበትን ገጽ የሚያሳይ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፤ ወይም
 • አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ከነበሩ የስጋ(Biological)ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ ዋናው የሰነድ ማስረጃ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ዋናው ማስረጃ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዋናው የሰነድ ማስረጃ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣

4.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ 
  በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና  
  ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት
  አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
   (ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture FORM)
5.ሦስት(3)የፓስፖርት መጠን (3x4cm)ያለውና ቢያንስ  ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
  የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
6.የአገልግሎት ክፍያ 275.20.00 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር/money order/
7.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
  ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP


 ለ.አካለ መጠን ላልደረሰ የኢትዮጵያ ተወላጅ ስለሚሰጥ አገልግሎት፣ 

1. ዕድሜው 18 ዓመት  ያልሞላው  የኢትዮጵያ  ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ  የተቀበለ  የውጭ  ዜግነት  ያለው ሰው ልጅ 
    በወላጅ  አማካኝነት  የሚከተሉት ሲሟሉ:-

        1.1  መጠየቂያ  ቅጽ-1  በሁለት  ኮፒ  መሙላት  (Click here to download)                  

        1.2  የታደሰ  የውጭ  አገር  ፓስፖርት  (አገልግሎቱ ቢያንስ  ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት) ዋናው  ሰነድ  ወይም  በኖታሪ ፐብሊክ
                የተረጋገጠ  ሁለት  ኮፒ ፣       
         
        1.3  የልጁ  የተረጋገጠና ሕጋዊ  የልደት የምስክር ወረቀት (በኖታሪ ፐብሊክ እና በሚመለከተው የውጭ ጉዳይ መ/ቤት በኩል የተረጋገጠ)
               ዋናው ከሁለት  ቅጅ  ጋር፣ 
       
       1.4   የወላጅ  የአገልግሎቱ  ጊዜው ያላበቃ የኢትዮጵያ  ተወላጅነት መታወቂያ  ካርድ ዋናው ሰነድ ወይም  በኖታሪ ፐብሊክ
                የተረጋገጠ  ሁለት  ኮፒ ፣               
        
        1.5  ሦስት(3)  የፓስፖርት  መጠን (3x4cm) ያለውና  ቢያንስ  ከ6ወር ወዲህ  የተነሱት ፎቶግራፍ  (ሁለቱ ጆሮዎች
                የሚታዩ፣ መደቡ  ነጣ ያለና ከጀርባው  ሙሉ  ስም የተጻፈበት)፣              

        1.6  ዕድሜያቸው 14 ዓመት  የሆናቸው፣ ከ14 ዓመት በላይና  18 ዓመት ያልሞላቸው  ልጆች  አሻራ  መስጠት ይኖርባቸዋል።  
               የጣት አሻራ  በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ 
               ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ  የጣት አሻራ መውሰጃ  ቅጽ/ form/  ላይ አሻራዎን ሰጥተው  ዋናውንና  ኮፒውን መላክ።
               ሆኖም  ድርጅቶቹ  የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው  በኩል የተዘጋጀውን  የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ
               መጠቀም ይችላሉ።    (ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture FORM)     
        
        1.7  የአገልግሎት  ክፍያ  27.52 የካናዳ  ዶላር  ለኢትዮጵያ  ኤምባሲ  የተፃፈ  መኒ ኦርደር/money order/
        1.8  አድራሻዎ  የተጻፈበት  ቅድሚያ  የተከፈለ  አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ  የካናዳ  ፖስታ  ወይም Tracking Number
                ያለው  (FEDEX ወይም UPS)  ከነቴምብሩ  አብሮ  መላክ፣
Top


  . የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ
     ካርድ ለሚጠይቁ፣

1.መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)
2.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወር የፀና የውጭ አገር
  ፓስፖርት ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
3.ከተሰጠበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ
  ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ (ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት ዓመት የፀና መሆን ይኖርበታል።)
4.መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ
  ነው። (Click here to download BOTH FORMS)  /ቅፅ-7/ እና /ቅፅ-8/
5.የባል ወይም የሚስት አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እና የትውልድ መታወቂያውን
  ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን
  ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
6.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት/ላት ግለሰብ ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን(3x4cm)ያለውና
  ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም
  የተጻፈበት)፣
7.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት/ላት ግለሰብ የጣት አሻራ ማቅረብ ይጠበቅበታል/ባታል።
  የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች
  ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው
  ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል
  የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
     (ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture FORM)፣
8.የአገልግሎት ክፍያ 275.20 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር/money order/፣
9.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
 
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP


መ.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ሲጠየቅ፣

 • የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 ዓመት የሚያገለግል ይሆናል። የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ እባክዎ በጊዜው መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ።
 • የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከ6 ወር በላይ ሳያሳድሱ ከቆዩ ያላሳደሱበትን ምክንያት የሚገልጽ ማመልከቻ አያይዘው ማቅረብ ይኖርብዎታል።
 • የአገልግሎት ዘመኑ እስካላበቃ ድረስ መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት ይችላሉ።
 • እባክዎ ከጉዞዎ ወይም ከታደሰ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ ከ45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል።      

1.መጠየቂያ ቅጽ-3 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)፣
2.የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና ሁለት ኮፒ፣
3.በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ማስረጃ፣

 • አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ወይም
 • የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ከነበሩ የስጋ(Biological)ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
  የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጵያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
  የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት
  ኮፒ፣ ወይም
 • ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍ/ቤት የተሰጠና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ መሆኑን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣

4.አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወር የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት
  ኮፒ፣
5.ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን(3x4cm) ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች 
  የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
6.በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ
  ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download BOTH FORMS) /ቅፅ-7
  እና /ቅፅ-8/
 በሁለት ኮፒ ተያይዞ ሲቀርብ፣
7.አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እና የትውልድ መታወቂያውን
  ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን
  ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
8.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
  በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን
  መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
  መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture 
  FORM)፣
ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና 
  አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅብዎትም።  
9.የአገልግሎት ክፍያ 275.20 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር/money order/፣
10.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
 
 ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP


ሠ.በጠፋ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ፣
1.መጠየቂያ ቅጽ-4 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)፣
2.መታወቂያው ስለመጥፋቱ በግለሰቡ የተጻፈ ማመልከቻ፣እንዲሁም ከተቻለ ስለመጥፋቱ የሚገልጽ ዝርዝር የፖሊስ
  ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
3.የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት(አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት) ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ 
  ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
4.የቀድሞ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ(የመታወቂያው ኮፒ ከሌለዎ መቼ እና ከየት እንደወሰዱት
  የሚገልጽ ማስታወሻ አያይዘው ይላኩ።)
5.ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
  የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
6.የጠፋው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ
  ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ(Click here to download BOTH FORMS)
 
/ቅፅ-7/ እና /ቅፅ-8/ በሁለት ኮፒ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እና የትውልድ
  መታወቂያውን ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች
 
ውስጥ አንዱን ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
7.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
  በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን 
  መላክ።ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
  መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።(ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture
   
  FORM)፣
 ከዚህ ቀደም የነበርዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ
  ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅብዎትም።  
8.ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን(3x4cm) ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
  የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
9.የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር/money order/ ሆኖ

    ሀ.በጠፋ ምትክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጥ 330.24 የካናዳ ዶላር፣
    ለ.በጠፋ ምትክ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰጥ  412.80 የካናዳ ዶላር፣
    ሐ.በጠፋ ምትክ ለሦስተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ሲሰጥ 550.40 የካናዳ ዶላር፣

10.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
 
 ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP


ረ.በተበላሸ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ፣
1.መጠየቂያ ቅጽ-4 በሁለት ኮፒ (Click here to download)፣
2.የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት (አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት) ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ 
  ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
3.የተበላሸው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውን ከሁለት ኮፒ ጋር፣
4.ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
  የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
5.የተበላሸው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር
  ጓደኛ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download BOTH
  FORMS) 
/ቅፅ-7/ እና /ቅፅ-8/ በሁለት ኮፒ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ
  እና የትውልድ መታወቂያውን ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር
  ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች
ውስጥ አንዱን ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
6.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
  በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን
  መላክ።ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ 
  መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።(ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture
  FORM)፣
 ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና
  አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅብዎትም።
7.ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ
  ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
8.የአገልግሎት ክፍያ 302.72 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር/money order/፣
9.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
 
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP


 

Notice and event announcement

 

 

It is Her Dam!!!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

“Today marks the beginning of the global virtual campaign to support the construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD).

 

We urge all Ethiopians and friends of #Ethiopia to join hands with the Campaign and to be Ambassadors of the #GERD by using the hashtags #ItsMyDam #እኔምለአባይአለሁ across Facebook, Twitter, LinkedIn and Instagram.

 

Post about the Dam, share all campaign content, and comment on GERD-related news. Let us spread the good news of the #RenaissanceDam.”

 

 

 

 

 

 

   

በካናዳ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ማህበራት በሙ:-

በወቅታዊ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ webinar (Zoom Meeting) ለመወያየት ... ለቅዳሜ ጁላይ 4/2020 ጥሪ ማስተላለፋችን ይታወቃል:: ሆኖም ስብሰባዉ ለሌላ ቀን በመተላለፉ ተለዋጭ ቀኑን በቅርብ የምናሳዉቃችሁ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን::

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ኦታዋ

 

I am here for Abay!  I am here for GERD!

I stand for Equitable use of the Nile Waters!

Please join the GERD Worldwide Virtual Campain from July 02-05,2020.

 

 

 

Happy Canada Day!

 

በካናዳ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

-------------------------------------------

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በማስመለከት በኢትዮጵያ ጉዳዩን የሚከታተሉ ከፍተኛ ባለሞያዎች፣ ኤምባሲው እና በካናዳ የሚገኙ ባለሞያዎች(Alliance for GERD in Canada) በመተባበር ግድቡ አሁን ያለበትን ሁኔታ፣ ከግድቡ ሙሌት እና አስተዳደር፣ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ እንዲሁም ከተሳታፊዎች በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ በwebinar(Zoom Meeting) በማድረግ ውይይት ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንገኛለን።

የውይይት መድረኩ በቅዳሜ እ.ኤ.አ. ከጁላይ 4/2020 በ10:00 a.m. Ottawa time (Eastern time) ለማድረግ የታቀደ ሲሆን የ Zoom ID እና Password ከስብሰባው በፊት እንደምናሳዉቅ እየገለጽን በዚህ ታሪካዊ መድረክ እንዲገኙ በአክብሮት ተጋበዛችዃል።

 

To all Ethiopians and Ethiopian Origins residing in Canada

--------------------------------------

The Embassy in cooperation with Higher Officials from Ethiopia and a Professional Group (The Alliance for GERD in Canada) Plan to Host a Webinar (Zoom Meeting) on Saturday July 4th 2020 at 10:00 a.m. Eastern time.

The discussion among other things would be pertaining to the current status of the Grand Ethiopian Renaissance Dam, the Filling and Operation of the dam and would attempt to address the questions and concerns of the Community with regard to the Tripartite Negotiation process. Accordingly, you are cordially invited to take part in this historic forum.

P.S. The Zoom ID and Password will be shared right before the conference.

 

 

 

 

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውሃ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር እንጂ ስለሺ በቀለ በኦታዋ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሪ ከሆኑት ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ለገሰ ሀይሌ፣ ከኤምባሲው ሰራተኞች እና በካናዳ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን Alliance for Great Ethiopian Renaissance Dam in Canada ከተባለ የባለሞያዎች ስብስብ ጋር ዛሬ እ.ኤ.አ በጁን 26/2020 በቪዲዮ ኮንፈረንስ በህዳሴ ግድብ ላይ ውይይት በማድርግ፤ ግድቡ የሚገኝበትን ደረጃ፣ የአገራችንን አቋም እና የመሳሰሉት ላይ ገለጻ በማድረግ ቡድኑ አገር ቤት ካለው አካል ጋር ተቀራርቦ በመስራት በሞያው አገራቸውን እንዲያገለግሉ እና የአገራቸውን ጥቅም ማሰጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊም ግድቡን በተመለከተ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአገሩ ጎን እንደሚቆም እና በመቀጠልም ዲያስፖራውን እንዲሁም አለም አቀፍ ማህበረሰብን የማንቃት እና የማነሳሳት ስራ እንደሚሰራ አሳውቀዋል፤ ቡድኑ በበኩሉ ከአገሩ ጎን በመቆም የአገራችንን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚሰራ እና በሞያ፣ በሞራል እንዲሁም በሚያስፈልግ ነገር ሁሉ ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

 

 

 

 

 

The African day is the Commemoration of the founding of the Organization of African Unity, established on May 25, 1963. On this day, many African Countries celebrate the hard-fought achievement of their freedom from European Colonial Powers.

 

On this day the #founding fathers established the OAU with objective among others to abolish slavery and help one other on the fight to end colonialism. A constant reminder of sacrifice, bravery, brotherhood and persistence. Happy African Day!

 

#Ubuntu

# I am because we are

#Africa we want to see

#the future is now

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ለካናዳ፣ በኢትዮጵያና በመላው አለም ለምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1441ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት ኤምባሲው ምኞቱን ይገልጻል።

The Embassy wishes the happiest 1441st Celebration of Eid Al- Fitr to all Muslims in Canada, Ethiopia and around the World.

 

 

 

 

 
For all Ethiopians, Ethiopian Origin in the diaspora and Freinds of Ethiopia
--------------------------------------------------------------------------------

In addition to the mechanisms of mobilization of resources for the prevention of the Corona Virus -COVID-19, Ethiotelecom has created a seamless platform to donate.

Please follow the link below and contribute your share in saving lives. 

 

 

 

Important Notice!!!In accordance with the Canadian Federal and Provincial authorities and the direction of our Government, the Embassy suspends all in-person Consular and Diaspora services starting from March 25, 2020 till further notice.All service requests shall be made to the phone numbers, emails or provided post address stated under:

For Consular Matters:

                         Ms. Tsehay Astale, Tel (343) 996 5643 and,

                         Mrs. Negisti Halefom, Tel (613) 262 1269

                     Email: consular@ethioembassycanada.org

For Diaspora Matters:

                           Mr. Abekrie Abdu, Tel (613) 302 5954

Email: diaspora@ethioembassycanada.org

For emergency and other matters:

                             Mrs. Frehiwot Kifle, Tel(613) 558 0286

Email: info@ethioembassycanada.orgPostal Address: 1501-275 slater st, Ottawa, K1P5H9

 

 

 

 

 

  በክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተላለፈ መልዕክት


በውጭ አገራት የምትኖሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባላችሁ የክረምት ዕረፍት ጊዜ በአገር ቤት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስክ እንድታገለግሉና የወደፊቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የበኩላችሁን የማይተካ ሚና እንድትጫወቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መልዕክት ተላልፏል፡፡

ስለሆነም፣ በዚህ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመሳተፍ የምትፈልጉ ወጣቶች በኤምባሲው በኩል በአካል በመቅረብ፣ በስልክ ቁጥር(613) 565 6637(የውስጥ መስመር 213) እና (613) 565 6637(የውስጥ መስመር 204) በመደወል እና በኢሜል አድራሻ merga.feyisa@ethioembassycanada.org እና fiseha.zerihun@ethioembassycanada.org ፍላጎታችሁን በመግለጽ እንድትመዘገቡ እያስታወቅን፣ መንግስት እናንተን በተቀደሰ ተግባር ላይ ለማሰማራት አስፈላጊውን ዝግጅት ያደረገ መሆኑን እንገልጻለን። 

የኢትዮጵያ ኤምባሲ 
ኦታዋ፣ ካናዳ
ሰኔ ፣ 2011 ዓ.ም.

 

INFORMATION REGRDING THE DIASPORA TRUST FUND

 

 Invitation for Bid

 

Name of Country: Ethiopia

 

Name of Project: Procurement of 400,000 MT wheat grain or milling wheat for Ministry of Trade and Industry (Ethiopian Trading Business Corporation).

 

Procurement Reference number: PPPDS/ETBC/ICB/PG/131/03/2011

 

 1. The Public Procurement and Property Disposal Service (PPPDS) on behalf of Ethiopian Trading Business Corporation have funds with the Procuring entity’s budget to be used for the Procurement of 400,000 MT milling wheat.
 2. The PPPDS invites eligible Bidders for the supply of goods and services mentioned above.
 3. Bidding will be conducted in accordance with the International Competitive Bid (ICB) procedures, contained in the Public Procurement and Property Administration Proclamation of the Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and is open to all Bidders from eligible source countries.
 4. Interested eligible bidders may obtain further information from PPPDS and inspect the bidding document at the address given below at 7(a) from 8:30 am to 5:30 pm until bid closing date.
 5. A complete set of bidding documents in English may be purchased by interested bidders at the address given below at 7(a) upon payment of a non-refundable fee of Birr 200.00 (two Hundred Birr) or equivalent amount in easily convertible hard currencyThe method of payment will be in cash.
 6. Bid must be delivered to the Address below at 7(b) on or before 31st January 2019 at 10:0 0 am.
 7. All bids must be accompanied by a bid security amount valued at 100,000 birror equivalent amount for each lot in the form of CPO or an unconditional Bank counter guarantee from domestic Commercial Banks. The bid security should be in the name of Public Procurement and Property Disposal Service. Bids will be opened in the presence of the bidders or their representatives who choose to attend the event at the address below at 7(b) at 10: 15 am on 31st January 2019.

 

(a) Documents will be issued at Ministry of Finance, compound No.2, block 5th, 1stfloor, room No. 101, Telephone 011-1-540524, 011-1-223755/22

 

(b) Bids must be delivered to, and will be opened at PPPDS, Ministry of Finance, compound No.2, Block No. 5th, 1st floor conference Hall.

 

PPPDS reserves the right to reject any or all bids and any items on the bid.

 

Public Procurement and Property Disposal Service (PPPDS)

 

Tel. 011-1-540524, 011-1-223755 or 011-1-223722

 

Website; http://www.pppds.gov.et

 

Addis Ababa, Ethiopia

 

 

 ለውድ ተገልጋዮቻችን በሙሉ፡-

 

ኤምባሲያችን በፓስፖርት፣ ቪዛና የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎቶች ላይ ባለው የምንዛሪ ልዩነት የዋጋ ለውጥ ያደረገ መሆኑን እየገለጸ አገልግሎቶቹንና የዋጋ ዝርዝር በተመለከተ በድኅረ ገጻችን Consular Section በሚለው ሜኑ ስር የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ

ኦታዋ ካናዳ

 

  

ለሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን

 

በካናዳ በጉዲፈቻ መንገድ የመጡ ህፃናትና ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሚሲዮናችን እነዚህን ዜጎች በማግኘትና ፍላጎት ያላቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እንዲሁም ያሉበትን ሁኔታ ኤምባሲው ለማወቅና ለመደገፍ ስለፈለገ ይህ መረጃ እንዲደርሳቸውና አድራሻቸውን እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

 

ስልክ ቁጥር (613) 565 6637 ext 204፣ 207፣ 213

 

ወይም በኢሜል፡ info@ethioembassycanada.org

 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ኦታዋ

 

 

Announcement Agraf

For all types of Visas /ለሁሉም ዓይነት የቪዛ ጥያቄ / 

Use online E-Visa:
https://www.evisa.gov.et/#/home
Announcement [ለውድ ተገልጋዮች!!] Agraf

ጉዳዩ፡ የውክልና ሰነዶችን የማረጋገጥ አገልግሎት አሰራር ላይ የተደረገ ለውጥን ይመለከታል፡፡
ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዛችሁ ተገልጋዮች ያዘጋጃችሁትን ውክልና ኖታሪ [ Notary] በማድረግ ብቻ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ የማረጋገጥ ስራ ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ከሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም [ ከጁን 21/2018] ጀምሮ ማንኛውም ወደ ኤምባሲያችን የሚላኩ ኖታሪ [ Notary] የተደረጉ የውክልና ሰነዶች ወደ ኤምባሲያችን ከመላካቸው በፊት እንደሌሎች ሰነዶች ኦታዋ በሚገኘው የካናዳ ግሎባል አፌየርስ [ Canadian global Affairs in Ottawa ] ከተረጋገጡ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ እንደሚኖርባቸው በአክብሮት መግለጽ እንወዳለን፡፡በሌላ በኩል የውክልና ሰነድ መስጠት ለሚፈልጉ ቫሊድ የሆነ የኢትዮጵያ ፓስፖርትና ትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ያላቸው ተገልጋዮች ኤምባሲው ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ሰነዱ ላይ በመፈረም በቀላሉ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡   

ቆንስላ አገልግሎት 

ለበለጠ መረጃ እባክዎ www.ethioembassycanada.org ይጎብኙ፡፡


 

USEFUL LINKS

EMBASSY OF ETHIOPIA
WASHINGTON DC, USA

WWW.ETHIOPIANEMBASSY.ORG


ETHIOPIAN CONSULATE GENERAL
LOS-ANGELES, LA, USA

WWW.ETHIOCONSULALA.ORG


ETHIOPIAN MISSION TO THE UN
NEW YORK, USA

WWW.ETHIOPIANMISSION-NY.ORG


MINISTRY OF FOREIGN AFFAIRS
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

WWW.MFA.GOV.ET

 


 

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com