•  እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡ በፓስታ የሚላኩ ማናቸውም ኮፒ ሰነዶች አገልግሎት ጠያቂው ባለበት ፕሮቪንስ በኖታሪ ፐብሊክ ስለ ትክክለኛ ቅጂነታቸው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል እንዲቻል ተወካዮች ውጭ ጉዳይ ቀርበው ጉዳይ ሲያስፈጽሙ ዋናውን የክፍያ ደረሰኝ ከዋናው የውክልና ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 • ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ከሆነ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካልዎት
  • ኤምባሲው ዘንድ በአካል የሚቀርቡ ከሆነ የውክልና ሰነዱን ኦፊሰሩ ባለበት ፈርመው ማስፈፀም ይኖርቦታል።
  • ውክልናው በመልዕክት / mail / የሚልኩ ከሆነ ውክልናውን በእንግሊዝኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ ካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር በመላክ አረጋግጦ ማቅረብ/መላክ
 • የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው እና አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት
  የሌላቸው
  ከሆኑ
  • ውክልናውን በእንግሊዝኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ ካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር በመላክ አረጋግጦ ማቅረብ/መላክ
  • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች እባክዎ መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡

የፖስታ አላላክ መመሪያ

 • በፖስታ ቤት አማካኝነት ውክልና የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው FEDEX ወይም UPS  ወይም ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ መሆን ይገባዋል፡፡
 • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡ 

 

ሀ. አትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው

ለ. ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ

ሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው ወይም አገልግሎቱ 
    የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው

 


 ሀ. የኢትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው

   መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1.  ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ

2.  የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ

3.  በካናዳ አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ማስረጃ  ኮፒ

             ሀ.ቋሚ የካናዳ መኖሪያ ፍቃድ ወይም

ለ. ቋሚ የካናዳ መኖሪያ ፍቃድ  ከሌለዎት የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያሳይ ማስረጃ ወይም

ሐ. የስራ ፍቃድ ወይም

መ. አንድ ፎቶግራፍና ፊርማ ያለበት ካሉበት ሐገር የተሰጠ መታወቂያ፣

4.  የአገልግሎት ክፍያ $ 85.32 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ

 •  መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/

5. ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ 
    Tracking Number ያለው FEDEX ወይም UPS  ወይም ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ
    ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ መሆን ይገባዋል፡፡

TOP 


 

 ለ. ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ

    መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1.  ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ

2 . የታደሰ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ

3.  አገልግሎቱ የፀና የካናዳ ፓስፖርት፣

4.  አንድ ፎቶግራፍና ፊርማ ያለበት ካሉበት ሐገር የተሰጠ መታወቂያ፣

5.  የአገልግሎት ክፍያ  $85.32 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ

 • መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/

6 . ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ
     Tracking Number ያለው FEDEX ወይም UPS  ወይም ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ
     ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ መሆን ይገባዋል፡፡

 TOP   
 


ሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ/በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ የሌላቸው ወይም

       አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው

    መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1.  በአማርኛና በእንግሊዘና ጽፈው ያዘጋጅቱን ውክልና በመጀመሪያ ባሉበት ፕሮቪንስ በኖታሪ ፐብሊክ 
    ቀጥሎ ኦታዋ በሚገኘው የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር በመላክ አረጋግጦ ማምጣት።

2.  ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ኮፒ፣

3.  አንድ ፎቶግራፍና ፊርማ ያለበት ካሉበት ሐገር የተሰጠ መታወቂያ፣

4.  የአገልግሎት ክፍያ $130.72 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ

 • መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
 • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/

5.  ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ
     Tracking Number ያለው FEDEX ወይም UPS  ወይም ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ
     ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ መሆን ይገባዋል፡፡

TOP

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com