ካናዳ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች
= = = = = = = = = = = = = = = = = =
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑት ክቡር ፍራንስዋ ፍሊኘ ሻምፓኝን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ክቡር አቶ ገዱ እንደገለፁት ኢትዮጵያና ካናዳ ከግማሽ ምዕተ- አመት በላይ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው ካናዳ በኢትዮጵያ ልማት ዙሪያ ጠንካራ አስተዋፅኦ ካደረጉ አገሮች አንዷ መሆኗን ገልጸዋል።

ክቡር አቶ ገዱ ኢትዮጵያ እያካሄደች ላለችው ሁለንተናዊ ለውጥ ካናዳ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንዲትቀጥል ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያና ካናዳ ከመንግስታት ትብብር ባሻገር በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ትብብራቸውን ማስፋት እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።

ክቡር አቶ ገዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አምስት ቀን ወደ ካናዳ የሚያደርገው በረራ ለሁለቱ ሀገሮች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መጠናከር የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለው አስታውሰው፣ ይኸው ይበልጥ እንዲጠናከር ሚኒስትሩ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ክቡር የካናዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንስዋ ፍሊኘ ሻምፓኝ በበኩላቸው ካናዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ፣ረጅምና ታሪካዊ መሰረት ያለው መሆኑን አንስተው፣ በቀጣይም ተባብሮ ለመስራት ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እያካሄደቸው ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም አድንቀው መጭው ምርጫም የተሳካ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀው፣ ካናዳ ኢትዮጵያ ለያዘቸው የለውጥ ጉዞ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማድረግም ካናዳ ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያና ካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በ1957 ዓ/ም መስርተዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com