የኢትዮ-ካናዳ የጋራ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ
====================================

በኢትጵያና በካናዳ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ፍሰት ይበልጥ ለማሳደግ አላማ ያደረገ የቢዚነስ ፎረም ዛሬ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ማህሌት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሁለቱ ሀገራት ከ1948 ዓም ጀምሮ ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ ጠንካራና ሁሉን አቀፍ የሆነ የሁለትዮሽ ትብብሮች መመስረት እንደቻሉ ገልፀዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ትብብሮችን ይበልጥ ለማጠናከር በርካታ ይፋዊ ጉብኝቶች መደረጋቸውን ጠቁመዋል። በሁለቱ ሀገራት መንግስታት መካከል ከተደረገው ያላሰለሰ ግንኙነት በተጨማሪ የቢዚነስ ትስስር መፍጠር መቻሉ የሀገራቱን ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር እንዳስቻለው ግልፀው፣ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በሁለቱም አገራት መካከል እምቅ የሆነ አቅም እንዳለም አምባሳደር ማህሌት ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ለባለፉት አስራምስት አመታት ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ማስመስገብ የቻለች ሀገር መሆኗንና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በመቅረፅ ወደ ትግበራ ተገብቶ እየተሰራበት እንደሆነ አብራርተዋል።፣ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙት አምስት ታላላቅ ኢኮኖሚዎች መካከል አንዷ ለማድግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ማህሌት ገልጸዋል። በንግግራቸው ጠቅሰዋል። አዲሱ አመራር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሉበትን ችግሮች መዋቅራዊ በሆነ መልኩ በመፍታት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር በቁርጠኛነት እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል። የካናዳ ባለሀብቶች በተለያዩ የማምረቻ ኢንዱስትሪ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩም አምባሳደር ማህሌት ጥሪ አቅርበዋል።
በካናዳን መንግስት የልዑካን ቡድንን በመወከል ንግግር ያደረጉት የካናዳ የውጭ ንግድ ስምምነቶች ማስፋፊያ ዳይሬክተር ሚስ ሲንዳይ ኢቭ ቦራሳ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ፣ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ሰሞኑን ክር ጠቅላይ ሚነስትር ጄስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ጉብኝት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ከፍተኛ ግንንኙነት እና ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል። የካናዳ ከፍተኛ የንግዱ ማህበረሰብም አባላትም በጉብኝቱ የተካተቱ በመሆኑ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር ትርጉም ያለው የቢዚነስ ለቢዚነስ ውይይቶች ለሶስት ቀናት እንደሚካሄዱ የገለፁ ሲሆን በሚቀጥለው ሰኞ የሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው እስካይላይ ሆቴል የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com