ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና ልዑካን ቡድናቸውን ዛሬ ማለዳ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ካናዳ በአያሌ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ እንደ ሆነች ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሚካሄዱትን ለውጦች እና ሪፎርሞች እንደሚያደንቁና እንደ ወዳጅ፣ ደግሞም እንደ አጋር በጎን ሆነው ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉም አውስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በዲሞክራታይዜሽን እና ሁለተናዊ ብልጽግናን በመገንባት ላይ ስለተመሠረቱት ባለብዙ ገጽታ ቀጣይ የሪፎርም ሥራዎች ገልጸዋል።

ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የጋራ ፍላጎት በሚስተዋልባቸው የልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ንግድ፣ የኢነርጂ ኢንቨስትመንት፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ መድኃኒት እና ተያያዥ ግብአቶች ላይ በጋራ ስለመሥራት ተወያይተዋል። የቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ በጋራ መሥራትንም አንዱ የትብብር አቅጣጫ አድርገው አንስተዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com