ወደ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት መዋቅር የሚደረግ ሽግግር ግልጽነትን ያረጋገጠ እና የሰራተኞችን መብት ከግምት ያስገባ መሆን አንዳለበት ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አሳሰቡ
=============================================

የአፍሪካ ሀብረት የመዋቅር ማሻሻያ የደረሰበትን ደረጀ በተመለከተ በተዘጋጀው ሪፖርት ላይ የህብረቱ አስፈጻሚ ምክር ቤት ውይይት አድርጓል። በቀረበው ሪፖርት ላይ የአባል አገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስተያየታቸውንም ሰጥተዋል።

የኢፊዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስርትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የህብረቱ የመዋቅር ማሻሸያ በመሪዎች ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግቡን እንዲመታ ግልጽነትን ባረጋገጠ መልኩ እና የሰራተኞችን መብት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መከናወን አንዳለበት አሳስበዋል። የህብረቱ የሰው ሃይል አደረጃጀት መወቅር ችሎታ እና ሃላፊነት ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሁም ልምድና ብቃትን ማዕከል ያደረገ መሆን እንዳለበት ያሳሰቡት ክቡር አቶ ገዱ ወደ አዲሱ መዋቅር የሚደረግ ሽግግር የሰራተኞችን መሰረታዊ መብትም ከግምት ያስገባ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com