የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፓርላማ ዋና ፀሃፊ ከሆኑት ሮበርት ኦሊፋንት የሚመራ የልኡካን ቡድን ጋር ዛሬ ጥር 08 ቀን 2012 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ውይይት አካሂደዋል። ወ/ሮ ሂሩት በዚህ ወቅት እንደገለፁት የኢትዮጵያ እና የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሁሉን አቀፍ በሆነ ትብብር ላይ የተመሰረተና ግንኙነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ መሆኑን ገልፀዋል። ካናዳ በአፍሪካ ቀንድ ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ላለው ያላቋረጠ ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር ያላትን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ቱሪዝም ይበልጥ ማስተሳሰር የሚቻልበት ሰፊና እምቅ አቅም እንዳለ ገልፀው ፤ ኢትዮጵያ ለግል ዘርፉ መስፋፋት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች በመሆኗ የካናዳ ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ወ/ሮ ሂሩት በዚህ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል። ሚስተር ሮበርት ኦሊፋንት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ልማት፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለውነ አስተዋጽኦ አድንቀዋል። ሚስተር ሮበርት በማያያዝም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃም ሰላም በማስከበር በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ አገር መሆኗን በማስታወስ ምስጋናችውን አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የምትከተለው ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄን መሰረት ያደረገ የችግር አፈታት መርህ ውጤታማ ዘዴ በመሆኑ ካናዳ እንደምትደግፈውም ገልፀዋል። ካናዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በንግድ፣ በኢቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፎች ይበልጥ ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኗን ገልፀዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com