================================================== 14ኛው የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔርሰቦች እና ህዝቦች ቀን በካናዳ ኦተዋ ከተማ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 11 ቀን 2020 በካናዳ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በተገኙበት "ህገመንግስታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል በደማቅ ዝግጅት ተከበረ። በበዓሉ ላይም ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ባስተላለፉት መልዕክት በአገራችን የተመሰረተው ህብረብሔራዊ የፌዴራል ስርዓት የአራችንን የብሔር፣ የቋንቋ እና የሀይማኖት ብዝሃነትን እንደ አገሪቷ ፀጋ እና ድምቀት በመውሰድ ጠንካራ አገራዊ አንድነት የመገንባት ዓላማ ያነገበ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የፌዴራል ስርዓቱ ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ሲደረግ በርካታ በጎ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማስቻሉን በማብራራት፤ ነገር ግን በሂደት የተለያዩ ውስንነቶች የነበሩበት መሆኑን መለየቱን አንስተዋል። በዚህም መንግስት በአሁኑ ወቅት የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን በማስቀጠል እና እጥረቶቹን በማረም እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ የፌዴራል ስርዓት ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ለዚሁ ዓላማ መሳካት ሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። በበዓሉ ላይ በኦተዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ የኢትዮጵያ ካሙዩኒቲ ተወካዮች የእንኳን አደረሳቹሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com