ጠ/ሚ ዐቢይ የሳተላይቷን መወንጨፍ አስመልክተው የደሰታ መልክዕት አስተላልፉ ----------------------------------------- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢቲአርኤስኤስ- 1 (ETRSS-1) የተባለችዋን ሳተላይት ወደ ሕዋ ማስወንጨፏን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሳተላይቷ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወነጨፈች መሆኗንና በቀጣይም ብዙዎችን ከኋላ የምታስከትል እንጂ የመጨረሻ እንደማትሆን ሙሉ ተስፋ አለኝ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ ሳተላይቷ በዕውቀትና በመረጃ በመንተራስ ግብርናውን ለማዘመን፣ በአፍሪካና በዓለም ገበያ ለመወዳደርና ውጤማ ለመሆን የምታግዝ፣ በድንበር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል፣ የአየር ፀባይ ሁኔታን ለመከታተል እንዲሁም በበቂ መረጃ ተመርኩዞ ውጤት ለማስመዝገብ መሰረት ሆና የምታገለግል ትሆናለች ብለዋል፡፡ ከአሁን በፊት ኢትዮጵያ ሳተለይት ስላልነበራት ምስሎችን ከሌሎች አገሮች ትገዛ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡ የሳተላይቷ አብዛኛው ወጪ በቻይና መንግስት የተሸፈን ሲሆን በቀጣይ ከሌሎች አገራት ጋር በመሆን አዳዲስ ሳተላይቶችን ለማምጠቅ እንደሚቻል ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በሳተላይቷ ዲዛይን ጀምሮ አስከ ምርት ድረስ የተሳተፉ ሲሆን፣ የቁጥጥር ማዕከሉም በአዲስ አበባ ላይ የተገነባ መሆኑን ዶክተር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ሕዋ የሚደረገውን የዕውቀት ፍለጋ ጉዞ የጀመረችበትና በቀጣይም በፍጥነት ሌሎች ሳተላይቶችን የምታስከትል መሆኗንን ገልጸው፣ ወደ ብልጽግና የሚደረገወው ጉዞ መጀመሩንና ሳያቋርጥ ለትውልድ በሚተርፍ መልኩ የሚረጋገጥ መሆኑን መግለፃቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ምልክታ ሳተላይት ታህሳስ 10/2012 አስወንጭፋለች። ሳተላይቷ ኢቲአርኤስኤስ 1(ETRSS-1) የሚል ስያሜ አላት። ሳተላይቷ ከቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ 400 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ነው የተወነጨፈችው። ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመገናኛና ቴክኖሎጂ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ለመስጠት የምትችል ሲሆን፤ የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ በእንጦጦ ኦቭዘርቫተሪና ምርምር ማዕከል ተገንብቶላታል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com