የዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ሽልማት የደስታ መግለጫ ፕሮግራም በካናዳ ተከበረ። =================================== ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ በካናዳ ኦተዋ ከተማ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች ከኢፌዲሪ ኤምባሲ ሠራተኞች ጋር በመሆን በጋራ ተከበረ። በዝግጅቱ ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ሽልማቱ ለአገራችን ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለውና በቀጣይ የበለጠ ስኬት ለማስመዝገብ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው በመግለፅ ሁላችንንም እንኳን ደስ አለን ብለዋል። በኦተዋ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች በበኩላቸው ሽልማቱ ታሪካዊ እና የአገራችን ስም በዓለም ደረጃ በበጎ እንድታወቅ እያደረገ መሆኑን በማስታወስ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። በተጨማሪም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ላከናወኑዋቸው ተግባራት እውቅና መሰጠቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው፣ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com