ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ የልኡካን ቡድን አባላትን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ባለፈው ግንቦት መጨረሻ ላይ በቫንኮቨር ካናዳ በተካሄደው የውመን ዴሊቨር አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደዚያው አቅንተው የነበሩት ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲንም መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱም በአጋርነት ሊሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡ ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ የመጡት የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ የስራ ሀላፊዎችም በቫንኮቨር የተደረገውን ውይይት መነሻ በማድረግ በቀጣይነት ሊሰሩ በሚችሉ ተግባራት ላይ ከፕሬዝደንቷ ጋር ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡ ከዩንቨርስቲው ጋር በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች እንደሚኖሩ የተናገሩት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለዚህም አጋርነት ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል፡፡ ሃላፊዎቹ በበኩላቸው እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ተባብረው ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው፡፡ከሌሎች አለም አቀፍ ዩንቨርስቲዎች ጋርም ትስስር እንዲፈጠር ለማድረግ የራሳቸውን አስተዋጽዎ እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

JSN Gruve is designed by JoomlaShine.com